• ቋንቋ
    • አማ
  • ቋንቋ
    • አማ
  • ቤት
  • ስለ ጎኅ
  • ምዝገባ
  • ያግኙን
  • ቤት
  • ስለ ጎኅ
  • ምዝገባ
  • ያግኙን

እንኳን ወደ ጎኅ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ ኅብረት ሥራ ማኅበር መጡ !

ያግኙን

ኑ፣በጋራ እንደግ!

ራዕይ

የቁጠባ ባህል እንዲዳብርና እንዲስፋፋ በማድረግ በተናጠል ሊወጧቸው የማይችሏቸውን ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ችግሮችን በተባበረ ጥረት በመወጣት ጎኅ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ ኅብረት ሥራ ማኅበር በአጭር ጊዜ ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር ነው፡፡

ኑ! 

ዓላማችን

 አባላት በተናጠል በመስራት ሊወጦቸው የማይችሏቸውን የኢኮኖሚና ማህበራዊ ችግሮችን በተባበረ ጥረት መወጣት፣መቋቋምና መፍታት፣

 አባላት ያላቸውን ዕውቀት ፣ሀብትና ጉልበት በማቀናጀት የተሻለ ውጤት ማግኘት፣ 

 በአባላት ዘንድ በራስ መተማመንን ማጎልበት፣ 

 በአባላት መካከል የቁጠባና ብድር አገልግሎት እንዲዳብርና እንዲስፋፋ ማድረግ 

 በአባላቱ በግል ይዞታ ስር ተበታትኖ የሚገኘውን ገንዘብ በቁጠባ መልክ በማሰባሰብ የአገሪቱ ማዕከሊዊ የገንዘብ ክምችት እንዲዳብር ማድረግ
 
 አባላት ስለ ገንዘብ ቁጠባና ብድር የኀብረት ሥራ ማኀበር ጠቀሜታና አገሌግልት ትምህርትና ስልጠና እንዲያገኝ ማድረግ 

 አባላትን በማቀራረብ እርስ በእርስ የመረዳዳትና የመተሳሰብ ልምድ እንዲያዳብሩ፣ 


 ለአባላትና ለአካባቢው ህብረተሰብ የስራ እድል መፍጠር፣

ለህልምዎ መሳካት ሁሌም ከጎኖ ነን

አባሎቻችን ከማህበሩ የተበደሩትን ገንዘብ አዋጭ በሆኑ በተጠኑ የስራ ዘርፎች እና የንግድ እድሎች ላይ እንዲያውሉት የምክር ና የስልጠና አገልግሎት እንሰጣለን፡፡

ተጨማሪ

ጎኅ ለደማቅ ተስፋ ለብሩህ ነገ !

የ ቤት ህልምዎ

የቤት ህልምዎን ለማሳካት በ ህብረት ስራ ማህበራችን ልዩ የቤት ቁጠባ ሂሳብ በመክፍት ይቆጥቡ የቤት ባለቤት ይሁኑ።

የ ልጅዎ የነገ ተስፋ

ለተሻለ የልጅዎ የነገ ብሩህ ተስፋ እና ስኬት በ ህብረት ስራ ማህበራችን የልጆች ቁጠባ ሂሳብ በመክፈት ህልሞን  እውን ያደርጋሉ።

የ ንግድ ሀሳብዎ

በ ህብረት ስራ ማህበራችን የ ንግድ ስራ ሀሳቦትን ከኛ ጋር  በመሆን በቀላሉ ህልምዎን ከስኬት ጫፍ ያደርሳሉ።

  • አገልግሎት
  • መስፈርት
  • ደንብ

ጎኅ ቁጠባ እና ብድር
 ሃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበር አገልግሎቶች

  • የነፍስ አዋቂ ቁጠባ
  • የልጆች/ሕፃናት ቁጠባ
  • የቤት ቁጠባ
  • የአጭር እና የረጅም ጊዜ ብድር
  • የስራ ፈጠራ ማማከር

ነፍስ አዋቂ ቁጠባ፡-
  መመዝገቢያ 350 ብር 
ወራዊ ቁጠባ 250 ብር

 ዝቅተኛ እጣ/ሼር/ 1000 ብር 
የአገልግሎት ክፍያ 1000 ብር
የቤት ቁጠባ፡- 
መመዝገቢያ 500 ብር
 ወራዊ ቁጠባ 350 ብር
 ዝቅተኛ እጣ/ሼር/ 3000 ብር 

የአገልግሎት ክፍያ 1000 ብር

ለ ነፍስ አዋቂ ቁጠባ፡-
 የትኛውም አባል ለመበደር 8(ስምንት) ወር ለተከታታይ ሳያቋርጥ መቆጠብ አለበት 
  ለመበደር ያሰበውን ብር/ገንዘብ/ በቁጠባ ደብተር ½(አንድ ሁለተኛ) መቆጠብ አለበት 
 የብድር ወለድ 13% (አስራ ሶስት ፐርሰንት) 
 የመመለሻ ጊዜ እንደሚበደሩት የብር መጠን የተለያየ ሰሌዳ ነው

ለ የቤት ቁጠባ፡- 
 የትኛውም የቤት ቆጣቢ ለመበደር 1(አንድ) አመት ሳያቋርጥ መቆጠብ አለበት 
  ሊበደር ያሰበውን ብር/ገንዘብ/ በቁጠባ ደብተሩ 1/3(አንድ ሶስተኛ) መቆጠብ አለበት 
  የብድር ወለድ 13.5% (አስራ ሶስት ነጥብ አምስት ፐርሰምት) 
  የብድር መመለሻ ጊዜ እንደተበደሩት ብር/ገንዘብ/ መጠን የተለያየ ሰሌዳ ነው

    ተጨማሪ ደንቦች

ያግኙን

አዲስ አበባ, አራዳ, ወረዳ 09, ስድስት ኪሎ, ቅዱስ ማርቆስ ቤተክርስቲያን

+251937591919
gohthefuture.gmail.com